በመኖርያ አከባቢ ተባዮችን መቆጣጠር
View this page in another language
English | Español (Spanish) | አማርኛ (Amharic) | العربية (Arabic) | 简体中文 (Chinese) | Français (French) | Hmoob (Hmong) | Oromo | Русский (Russian) | Somali | Tiếng Việt (Vietnamese)
ቤትዎ ውስጥ ተባዮችን ለመቆጣጠር ጥረት ሰያደርጉ :
- በአትክልት ወይም በግብርና ቦታዎች ጸረ ተባይ አይጠቀሙ፡፡
- በዚህ የተመረቱ ወይም ”በልምድ የተቀነባበሩ ” ወይም ፍቃድ ከሌለው ሰው የሚሸጡ ምርቶች አይጠቀሙ፡፡
በቤት የተባይን መቆጣጠርያ ውጤታማ መንገድ ኬሚካል መጠቀምና በ ፔስ ማኔጅመነት ፕሮፌሽናል(PMP) የሚዘጋጀው የሙቀት ህክምና መጠቀም ነው፡፡ ስለዚህ በራስዎ መንገድ ተባይን እንዴት መቆጣጠር እንደሚችሉ መረጃ እየሰጠንዎት ነው፡
ተባዮቹን በራስዎ ጥረት መቆጠጣር ከባድና ጊዜም የሚፈጅ ነው፡፡ ዕቃዎችን፣ የቤት ዕቃዎችና የግል ቁሳቁሶችን ማንቀሳቀስ ይጠይቃል፡፡ እያንዳንዱ ክፍል እንዴት እንደሚያጸዱ ዕቅድ ያውጡ፡፡ “ንጹህ ቦታ” ያዘጋጁ፡፡
ተባዮችን በእጅ መግደል 100% ውጤታማ አይደለም፣ ይሁን እንጂ በቤትዎ ውስጥ ሚገኙ ተባዮችን ለመቀነስ ያግዝዎታል፡፡ ይዘው ሊጨፈልቋቸው ይችላሉ ወይም በስትኪ ቴፕ ይዘው ሊጥሏቸው ይችላሉ፡፡
ተባዮችን ለማደን የሚያገለግሉ መሳርያዎች፡ መብራት፣ ያገለገ ካርድ( ወይም መሰል ነገር) ንጹህ ታፕ (tape)፣ ፕላስቲክ ቦርሳ፣ ጨርቅና ሙቅ ውሃና ናቸው፡፡
ደረጃዎች: ተባዮቹን ለመፈለግ መብራትና ክረዲት ካርድ ይጠቀሙ፣ ካርዱን በቀዳዳዎችና ከፍት ቦታዎች በማንቀሳቀስ ተባዩቹን ለመግፋት ይጠቀሙበት፡፡ .ተባዮቹን ለመያዝ ስቲኪ ታፕ( sticky tape) ይጠቀሙ፡፡ የተበከሉ፣ ተባዮች፣ የተጣሉ፣ እንቁላሎችና ሸድ ስኪንስ( shed skins) ማጽደት ሙቅ ውሃን ይጠቀሙ፡፡
ክፍት ማድረግ በፍጥነት ተባዮቹን ለመያዝ ያግዛል፡፡ በቤዝ ቦርዶች፣ የኤሌክትሪክ ቁሳቁሶች( እንደ ቴለዚዥንና ስቴሬስ) ያሉ እንዲሁም እንደ አልጋ፣ ሶፋ፣ የአልጋ ፍሬሞች እና ተሳቢዎች ያሉ ተባይን ሊደብቁ የሚችሉ ክፍት ያድርጓቸው፡፡ ባዶ ሲሊንደር የሚጠቀሙ ከሆነ ወዲያውኑ ዕቃዎቹ ወደ ፕላስቲክ ቦርሳ ጨምረው ዘግተው ይጣሉት፡፡ ባዶ የሆነውን ዕቃ ያጽዱት፡፡ ባዶ ዕቃ ከቦርሳ ላይ የሚጠቀሙ ከሆነ ወዲያው ቦርሳወን በማስወገድ ፕላቲኩን ለማስወገድ ይዝጉት፡፡ ባዶ ዕቃው ምንም ዓይነት የቀረ ነገር እንዳይኖረው ይመልከቱት፣ የቀሩ ካሉ እንዳይስፋፉ ይግደልዋቸው፡፡
ማጠብ ቁሳቁሶች በማሽን ወይም ማድረቅያ በማስቀመጥ የሚደረግ በጣም ውጤታማ ነው፡፡ የቆሻሻ መከላያ( linens) እና የቆሸሹ ልብሶች ተባይ የማስፋፋት ዕድላቸው ለመቀነስ እስከሚታጠቡ ተሰብስበው በፕላስቲክ ቦርሳ ውስጥ መታሸግ አለባቸው፡፡ ልብሱ የሚቋቋመውን ያህል በከፍተኛ ሙቀት አጥበው ያድርቁት፡፡ ካልታጠበ ለ30 ደቂቃዎች ያህል ዕቃው በሚቋቋመው ያህል በከፍተኛ ሙቀት ይጠቡት፡፡
እንፋሎት በአግባቡ ከተተገበረ በጣም ውጤታማ ነው፡፡ ማሞቅያ ከአንድ 1 ጋሎን አቅም ይጠቀሙ፣ ከመጠን መቆጣጠርያ ቢሆን ይመረጣል፡፡ ወለል ወይም ሶፋ የዕቃው ጨርቅ እንዲለቅ ያስችላል፡፡ ተባዮች ውጤታማ በሆነ መልኩ ለመግደል የእንፋሎት ብሩሽ ካለፈ ወዲያው የምድር ቤቱ ሙቀት ከ160-180°F መሆን አለበት፡፡ ሙቀቱን ለመቆጣጠር ኢንፍረሬድ ቴርሞሜትር ይጠቀሙ፡፡ እንፋሎት የእሳት ቃጠሎ ሊያስከትል ስለሚችል በጥንቃቄ ይጠቀሙ፡፡
የተበከሉ ነገሮችን ማቀዝቀዝ(Freezing )ተባዮችን ለመግደል ቀላሉ ነገር ነው፡፡ ለተወሰነ ጊዜ ማቀዝቀዝ ነው የሚያስፈልገው፡፡ በማቀዝቀዝ ተባዮቹን ለመግደል ቁሳቁሶቹ በማቀዥቀዣ ለ4 ቀናት በመተው ከ0oF በታች በሆነ መጠን ማስቀመጥ ያስፈልጋል፡፡ ለሚያቀዘቅዙት ነገር ይጠንቀቁ፣ ማቀዝቀዝ ውድመት ሊያስከትል ይችላል፡፡
የፍራሽ ማስቀመጫ ለተባዮች ቀዳሚ ተመራጭ በሆነና ለመያዝ በሚያስቸግር ቦታ እንዳይቀመጡ ይከላከላል፡፡ የፍራሽ ማስቀመጫው ከተበከለ ይሸፉኑትና ከ2 ሳምንት በኃላ መሞት ይጀምራሉ ፣ ነገር ግን ቢያንስ ለ18 ወራት ተሸፍኖ መቆየት አለበት፡፡ ካብዚ ብተወሳኺ አዲስ የመበከል ችግር ከታየ የፍራሽ ማስቀመጫው በቀላሉ ማጽዳት ይቻላል፡፡ ተባዮቹን ለመሸፈን የሚዘጋጀው የፍራሽ ማስቀመጫ የተባይ መስፋፋት ይቀንሳል እንጂ አያቁምም፡፡
የደረቅ ሙቀት ዘዴ ውጤታማ የተባይ መቆጣጠርያ ነው፡፡ ይህ ዘዴ የተበከሉ ቁሳቁሶችና ክፍሉ ተገቢ ሙቀት አግኝተው ተባዩን በውጤታማነት ለመከላከል በተባይ አስተዳደር ባለ ሙያ ብቻ መደረግ አለበት፡፡ ራስዎን በሙቀት ለማጽዳት እንዳይሞክሩ፡፡
ጸረ ተባዮች የግል ተባዮች ከተጠቃው ዋናው ቦታ ወደ ሌላ ቦታ የሚንቀሳቀሱ ስለሆነ ጸረ ተባዮች ተባዮቹን ለመቆጣጠር ጠቃሚ ናቸው፣ ጸረ ተባዮች በጥንቃቄና በሚገባ ይጠቀሙ፡፡ ተገቢውን ጸረ ተባይ ጥቅም ላይ ለማዋል የተባይ አስተዳደር ባለ ሙያ እንዲቀጥሩ በአጽንኦት ይመከራሉ፡፡ ለሌላ ተባይ የተዘጋጀ ጸረ ተባይ ለመጠቀም አይሞክሩ፣ ምክንያቱ ተባዮቹን ወደ ሌሎች አከባቢዎች እንዲስፋፉ ሊያደርግ ይችላል፡፡