የተባይ አስተዳደር ባለሚያ መቅጠር

ተባዮችን ለማጥፋት በጣም ውጤታማ አገባብ የተባይ አስተዳደር ባለሙያችን መቅጠር (PMP) ነው፣ ይህ በብዛት “ የተባዮች አጥፊ (Exterminator)” ተብሎ ይታወቃል፡፡  በራስዎ መንገድ ተባዮችን ለመቆጣጠር ጥረት ካደረጉ ስኬታማ አይሆኑም፡፡ PMP ሲፈልጉ የተወሰነ ጊዜ ወስደው ጥናት ያድርጉና ጥሩ ኩባንያ ያግኙ፡፡ በርካሽ ዋጋ የሚገኘው የተሻለ አማራጭ ላይሆን ይችላል፡፡

የተባይ አስተዳደር ባለሙያ ፍለጋ

  1. በአገራዊ ፔስ ማኔጅመነት ማህበር ይፋዊ ድረ ገጽ በሆነው www.pestworld.org ላይ ፈልግ ( Find a pro ) በሚለው በማሰስ በአከባቢዎ የሚሰራ PMP ይፈልጉ፡፡
  2. በሚኒሶታ የንግድ አደረጃት ቁጥጥር እንዲያደርግ ሚኒሶታ የግብርና ክፍል (MDA) ፈቃድ ሊሰጠው ይገባል፡፡ ፈቃድ ያላቸው የተባይ ቁጥጥር አደረጃጀቶች በሚኒሶታ የግብርና ክፍል ድረ ገጽ: www2.mda.state.mn.us/webapp/lis/pestappdefault.jsp ተዘርዝረዋል፡፡
  3. የስልመጽሃፍ ቢጫ  ገጾችን (phonebook Yellow Pages )ከ“ተባይ” የሚለውን ስር ይመልከቲ; ከጓደኛ ወይም ጎረቤት ምክር ያግኙ

እነዚህን ኩባንየቀወች ይጠንቀቁለየተባይ አስተዳደር ባለሙያችን  የሚጠየቁ ጥያቄዎች

 ሲፈልጉ የሚከተሉትን ጥያቄዎች እንዲጠይቁ እንመክርዎታለን :

  • ከሚኒሶታ የግብርና ክፍል ስልጠና የወሰዱ ናቸት ው?  ስራ ከመጀመርዎ በፊት የተሰጠው የMDA እንዲሳይ ይጠይቁት፡፡ በሌሎች ስቴቶች፡ የግብርና ክፍል ያረጋግጡ፡፡
  • ኩባንየዎ የተጠያቂነት ኢንሹራንስ አለው?
  • ኩባንየዎ ከአገራዊ የተባይ አስተዳደር ማህበር አግንኙነት አለው? ( NPMA  ለሚከታተለቸው አባላት በጣም ጥሩ የሆነ የአስተዳደር መተግበርያ አዘጋጅቷል)፡፡
  • ኩባንያው ከሌሎች ቅሬታ የሚቀርብበት እንደሆነ ለማወቅ በበለጠ የቢስነስ ቢሮ (Better Business Bureau) ያረጋግጡ፡፡
  • ኩባያው ተባዮቹን በማሰስና መድሃኒት በመርጨት ምን ያህል ልምድ አለው ?  ሰራቶቹ ምን ዓይነት ስልጠና ያገኛሉ? ለምን ያህል ጊዜ?ኩባንያው በተባይ የተጠቁ ቦታዎች ለማጽዳት ውል ለማድረግ የሚጠቀምባቸው ስታንዳርዶች ምንድ ናቸው ?
  • የማጽዳት ቆይታው ለምን ያህል ጊዜ ይቆያል?
  • በማጽዳት ሂደቱ  የእርስዎ(የደንበኛው ኃላፊነቶች ምንድ ናቸው)?
  • ጉብኝቶች የሚቀጥሉ እንደሆነ PMP ይጠይቁ፣ ከመነሻ የማጽዳት ሂደት በኃላ፤ የአስተዳደር ዕቅድ አካል ናቸው ?
  • የማጽዳት ሂደቱ ከታቀደ ኩባንያው ጸረ ተባይም ይጠቀማል ?
  • ተባይ የማጽዳት ሂደት በሚከናወንበት ወቅት ምን ዓይነት የደህንነት መከላከያዎች ያስፈልጋሉ?  

ተጨማሪ መረጃ

  • ውጤታማ የጸረ ተባይ መድኃኒት ሶስት ዓይነት ሊያስፈልግ ይችላል: የተወሰነ ቆይታ ያላቸው   ከሚካሎች( residual chemicals)፣ ወዲያው ጥቅም ላይ የሚውሉ  (ከተባዮች ጋር የሚገናኙ ኬሚካሎች) እንዲሁም ድቄት (ከሰዎች እንቅስቃሴ ራቅ ብለው ለሚገኙ ተባዮች የሚቀባ).

ውሉን መከለስ

መቅጠር የሚፈልጉት የተባይ ተቆጣጣሪ ኩባንያ ከመረጡ በሚከተሉት ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርገው ውሉን በጥንቃቄ ይመልከቱት:

  • የኩባንያ ስም፣ አድራሻ፣ ኩባንያው የሚገኝበት አስራሻ
  • የሚከናወኑ  ዝርዝር ተግባራት
  • የሚተገበሩ የተባይ ማጥፋት መንገዶች
  • መከተል ያለብዎት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች
  • የሚጀመርበት/ የሚያበቃበት ቀን  እንዲሁም የክትትል ጉብኝቶች(አስፈላጊ ከሆነ)
  • የኩባንያው የፈቃድና የኢንሹራንስ ሽፋን
  • የማይካተቱ ነገሮች፣ የመሰረዝ ፖሊሲ እንዲሁም ግጭቶችን ለመፍታት የዳኝነት አንቀጽ
  • ዋስትና
  • ዋጋ

ጸረ ተባይ መድሃኒቶች የሚረጩ ከሆነ የምርት ደረጃና የዕቃው የደህንነት ዳታ መረጃ(MSDS) ቅጂ እንዲሰጥዎት መጠየቅ ይችላሉ፡፡ አገባብ ያላቸው የተባይ ተቆታጣሪ ኩባንያዎች እነዚህን ሰነዶች አቅርበው እንደ አንድ የአግልግሎት ውል አካል ከደንበኞቻቸው ይመለከትዋቸዋል፡፡

ተባዮቹን ለማጽዳት መዘጋጀት

ተባዮቹን የማጥፋት ስራ ከመጀመሩ በፊት በPMP የሚሰጡ መመርያዎችን ይተግብሩ፡፡ እነዚህን መመርያዎች መከተል ተባዩን ለማጥፋት በጣሚ ሊሆኑ ይችላሉ፡እነዚህ የሚከተሉትን ሊያካትቱ ይችላሉ:

  • ልብሶችና አልጋ ልብሶችን ማጠብ
  • ቆሻሻን መቀነስ፣ ሁሉም ቁሳቁሶች ከምድር ቤት ማንሳት
  • በቤትዎ ጥገናዎችን ማድረግ
  • የክፍሉን ጫፍ ተደራሽ ለማድረግ ዕቃዎችና ቁሳቁሶችን  ያንሱ
  • ቁም ሳጥኖች፣ ጠረጴዛዎችና ተሳቢዎች ባዶ ያደርጓቸው
  • ፍራሾችና ቦክስ ስፕሪንግ ይሸፍንዋቸው

የተባይ አስተዳደር ባለሙያው ስራው ከጨረሰ በኃላ የሚያሳስብዎ ነገር ወይም ጥያቄ ካልዎት ወደ ኩባንያው ይወደውሉ፡፡

Contact Us

For more information contact the bed bug InformationLine:
bedbugs@umn.edu

Now Available in over 100 Languages!


What NOT to do button